Nehmen Sie an unserer Lesesitzung teil. Lesen Sie die Geschichte auf unserer Facebook-Seite. Kommen Sie ins Goethe-Institut. Teilen Sie Ihre Lesung mit. Kommentiere Ihre Erfahrung.
Weitere Informationen finden Sie auf unserer Facebook-Seite.
https://www.facebook.com/goethe.addisabeba
Die Sizung findet in Amharich statt.
ኑ! ንባብን እንካፈል
የንባብ አንዱ ትርፍ ስላነበቡት ነገር ከሌሎች ጋር ማውራት መቻል ነው፡፡ የሌላውን ምልከታ መጋራት፣ ምልከታውን መሞገት፣ ከእዚያ ውስጥ አዲስ ምልከታን መውለድ፡፡ ይህንን ሁለት ሶስት ሆኖ ከማድረግ በዘለለ በርከት ብሎ ማድረግ የሚቻልበት መድረክ በከተማችን ማግኘት ቀላል አይደለም፡፡ የጀርመን ባህል ማዕከል በእዚህ በኩል የራሱን አስተዋፅዖ ሊያበረክት እንዲህ ይለናል!
ከየካቲት ወር ጀምሮ በየሁለት ወሩ ከጠዋቱ 9.30 እስከ 11.30 ሰዓት ልንገናኝ ፕሮግራም ዘርግተናል፡፡ የፌስ ቡክ የመጽሀፍ ክበብ መስርተን የተለያዩ የሥነ ጽሑፍ ስራዎች ላይ ያለንን ንባብ ልንካፈል፡፡ እርሰዎ የእዚህ ፕሮግራም ተካፋይ መሆን ከፈለጉ በፌስቡክ ገፃችን ላይ የምንለጥፈውን አጭር ታሪክ ያንብቡ፡፡ ካነበቡ በኋላ ንባብዎን ማካፈል ከፈለጉ፣ የፌስቡክ ገፃችን ላይ መገኘት እንደሚፈልጉ ኮመንት በመፃፍ ያመልክቱ፡፡ በፕርግራሙ ላይ እንዲገኙ የሚፈቀደው ቁጥር ከ 20 መብለጥ ስለሌለበት፣ የምንጋብዘው የመጀመሪያዎቹን 20 ፈቃደኞች ብቻ ይሆናል፡፡
Zurück