የአውሮፓ ህብረት

የአውሮፓ ህብረት በአውሮፓ ሃገር ውስጥ የብዙ ሃገራት ህብረት ነው። ከአራት ሚሊዮን ካሬ ኪሎ ሜትር በላይ በሆነ ቦታ ወደ 450 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ይኖራሉ። የአውሮፓ ህብረት በአሁኑ ወቅት 27 አባል ሀገራት አሉት። እነኝህ ሀገራት በአውሮፓ ውስጥ ለሁሉም ሰዎች ሰላም፤ ትብብር እና ብልጽግና ይፈልጋሉ፡፡ ሁሉም አውሮፓውያን ጥሩ ኑሮ ምመኖር አለባቸው። የአውሮፓ ህብረት ህይወትን የተሻለ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ቀላል ማድረግ አለበት። የአውሮፓ ኅብረት ሀገራት እርስ በርስ ችግሮችን እንዲፈቱና በትብብር እንዲሠሩ ፣በጋራ ደንቦች እንዲኖሩ ይረዳል።

Audio-Player: Artikel anhören

Artikel anhören

Die Europäische Union

Europäische Flagge © Goethe-Institut/ Gina Bolle

አስተዳደር

24 ብሔራዊ ቋንቋዎች አሉ። ሁሉም የአውሮፓ ህብረት ሰነዶች እና መረጃዎች የተፃፉት በእነዚህ ቋንቋዎች ነው። ለአውሮፓ ህብረት ሥራ አስፈላጊ አካላት አሉ፡፡ እነሱም የአውሮፓ ፓርላማ ፣ የአውሮፓ ኮሚሽን ፣ የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት እና ሌሎችም ናቸው።

ታሪክ

የአውሮፓ ህብረት የተመሰረተው ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ነበር፡፡ ጀርመን እና ሌሎች አምስት አገሮች የመጀመሪያውን የአውሮፓ ማህበረሰብ በ1951 መሰረቱ። በአውሮፓ ጠንካራ ኢኮኖሚ እንዲኖር ይፈልጉ ነበር። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የአውሮፓ ህብረት ተለውጧል፡፡ ከ2002 አ ም ጀምሮ አንድ የጋራ ገንዘብ፣ ዩሮ አለ። በ 20 የአውሮፓ ህብረት አገሮች ውስጥ ሰዎች በዩሮ ይከፍላሉ፡፡

ግቦች እና እሴቶች

የአውሮፓ ህብረት የጋራ እሴቶች ያለው ማህበረሰብ ነው። እነዚህም ሰላም፣ ዲሞክራሲ፣ ነፃነትና የሁሉም ህዝቦች እኩልነት ናቸው። እሴቶች ትክክል እና ስህተት የሆነውን ያሳዩናል፡፡ ትክክለኛውን ነገር እንድናደርግ ይረዱናል፡፡

የአውሮፓ ህብረት ግቦች ለምሳሌ አካባቢን መጠበቅ እና ኢኮኖሚን ማጠናከርን ያካትታሉ። በአውሮፓ ውስጥ ያሉ ሰዎች ደህና መሆን አለባቸው፡፡ ወንድ ይሁኑ ሴት፣ ከየትም ሃገር ይምጡ ወይም የትኛውም ሃይማኖት ይኑው ሁም ሰዎች በእኩልነት መታየት አለባቸው።

በአውሮፓ ህብረት ውስጥ ሁሉም ሰው በእኩል መታየቱን የሚቆጣጠር አካል አለ፡፡ ማንም ሰው ለምሳሌ በዘሩ፣ በሃይማኖት፣ በጾታ ወይም በአካል ጉዳት ምክንያት መበደል የለበትም። የእኩልነት አያያዝ ቢሮ ሰዎችን ይረዳል። መረጃዎች እና ምክር በተለያዩ ቋንቋዎች ይገኛል።

በአውሮፓ ህብረት ውስጥ ተንቀሳቃሽነት

በአውሮፓ ህብረት ውስጥ ያሉ ሰዎች ከአንዱ ሀገር ወደ ሌላ ሀገር በቀላሉ መጓጓዝ ይችላሉ። ከአውሮፓ ህብረት ሀገር የመጡ ከሆነ በአውሮፓ ህብረት ሀገራት ውስጥ በነፃነት መንቀሳቀስ ይችላሉ። በሌላ የአውሮፓ ህብረት ሀገር መኖር፣ መስራት ወይም መማር ይችላሉ።

የመጡት የአውሮፓ ህብረት አባል ካልሆነ ሀገር ነው? እርስዎ የሶስተኛ ሀገር ዜጋ ነዎት። እርስዎም በአውሮፓ ህብረት ውስጥ መጓዝ፣ መኖር እና መስራት ይችላሉ። ነገር ግን ለዚህ ልዩ ህጎች አሉ፡፡ ለምሳሌ በአውሮፓ ህብረት ውስጥ ለአንድ የተወሰነ ሀገር የመኖሪያ ፍቃድ ያስፈልግዎታል፡፡ እዚያ ለብዙ ዓመታት መኖር ይኖርቦታል እና እራስዎን በጥሩ ሁኔታ ማስተዳደር መቻል አለብዎት። ከዚያ ለፈቃድ ማመልከት ይችላሉ፡፡ በዚህ ፈቃድ ወደ ሌሎች የአውሮፓ ህብረት ሀገሮች መሄድም ይችላሉ።

ተከተሉን