አገር ማስለመጃ ትምህርት

Ein Tisch mit Begriffen auf Karten zum Zuordnen © Goethe-Institut/ Gina Bolle

ለጀርመን አዲስ ኖት እና ቋንቋውን መማር ይፈልጋሉ? እንግዲያውስ የውህደት ኮርሱን መከታተል ይችላሉ። ትንሽ ጀርመንኛ አልያም በጭራሽ መናገር የማይችሉ ከሆነ ቋንቋውን መማሮት ግድ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ማለት የውህደት ኮርሱን መውሰድ አለብዎት ማለት ነው። የኢሚግሬሽን ባለስልጣን ይህንን መረጃ ይሰጥዎታል።

ተሳትፎ

የኢሚግሬሽን ባለስልጣን ኮርሱ ላይ ለመሳተፍ ፈቃድ እና የቋንቋ ትምህርት ቤቶች ዝርዝር ይሰጥዎታል። ከዚያም በአቅራቢያዎ የሚገኝ የቋንቋ ትምህርት ቤት ይመርጡና ከዚያ መመዝገብ ይችላሉ፡፡አንዳንድ የቋንቋ ትምህርት ቤቶችም በበይነ መረብ ኮርሶችን ይሰጣሉ።

የሁሉንም የቋንቋ ትምህርት ቤቶች ከዚህ "ጠቃሚ አድራሻ" ስር ማግኘት ይችላሉ። በዚህ አደራሻ ስር በአካባቢዎ ያሉ ትምህርት ቤቶች መፈለግ ይችላሉ፡፡ እንደ አድራሻ ወይም ስልክ ቁጥር ያሉ መረጃዎች በካርታው ላይ ማየት ይችላሉ።

ምደባ, ወጪዎች, የትምህርት ሰዓቶችና ፈተና

ከተመዘገቡ በኋላ፣ ከትምህርት አቅራቢው ጋር የቅድመ እውቀት ፈተና ይወስዳሉ። ይህ ፈተና ከእርስዎ ብቃት ጋር የሚመጥነውን የቋንቋ ስልጠና በትክክለኛው መንገድ እንዲያገኙ ይረዳዎታል፡፡ ለናንተ የሚወጣው ወጪ አብዛኛውን ጊዜ ለአንድ የትምህርት ክፍለ ጊዜ 2.29€ ነው። ሁሉም ተማሪዎች ለትምህርቱ የመክፈል ግዴታ የለባቸውም። ተጨማሪ መረጃ ከፌደራል የስደተኞች ቢሮ ማግኘት ይችላሉ። የውህደት ኮርስ የቋንቋ እና ግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርትን ያካትታል።

የመደበኛ ቋንቋ ኮርስ 600 የትምህርት ክፍለ ጊዜ አለው። በእነዚህ ሰአታት ውስጥ እንደ ግብይት፣ ኑሮ፣ ልጆች፣ ሚዲያ፣ የመዝናኛ ጊዜ፣ ትምህርት ቤት እና ስራ ወይም ዶክተርን መጎብኘት ጋር የተገናኙ ርእሶች ይማራሉ።

መጨረሻ ላይ የመጨረሻውን ፈተና ("የጀርመን የስደተኞች ፈተና") ይወስዳሉ፡፡ ከፈተና በኋላ "የተማሩበትን የምስክር ወረቀት " ያገኛሉ። ከዚያ ጀርመንኛን በደረጃ A2 ወይም B1 መናገር፣ ማንበብ እና መፃፍ ይችላሉ። ብዙ የስራ ቀጣሪዎች ይህንን የምስክር ወረቀት ማየት ይፈልጋሉ። እንደ ኢሚግሬሽን ቢሮ ባለ ቢሮ ውስጥም አንዳንድ ጊዜ ያስፈልገዎታል። ዜግነት ማግኘት ከፈለጉ የኮርሱ የምስክር ወረቀት ጠቃሚ ነው።

ከቋንቋው ትምህርት በኋላ፣ የአድማስ ማስፊያ ትምህርት ይወስዳሉ። የአድማስ ማስፊያ ትምህርቱ 100 የትምህርት ክፍለ ጊዜያት አሉት፡፡ በነዚህ ሰዓታት ውስጥ ስለ ጀርመን የህግ ስርዓት፣ ታሪክ እና ባህል ብዙ ነገሮችን ይማራሉ። በህብረተሰብ ውስጥ እሴቶች እና አብሮ መኖር ዋነኞቹ ጠቃሚ ርዕሰ ጉዳዮች ናቸው፡፡ መጨረሻ ላይ "በጀርመን መኖር" በሚል የመጨረሻውን ፈተና ይወስዳሉ፡፡

የመጨረሻውን ፈተና አላለፉም? ተጨማሪ የ 300 ሰዓታት ትምህርቶችን ማግኘት ይችላሉ፡፡ ፈተናውንም እንደገና መውሰድ ይችላሉ፡፡

ልዩ የውህደት ኮርሶች እና ሙያዊ ቋንቋ ኮርሶች

ዕድሜያቸው እስከ 27 ዓመት ለሆኑ ወጣቶች ልዩ አገር ማስለመጃ ትምህርት አለ፡፡ ትምህርቱ የሙያ ስልጠና መውሰድ ከፈለጉ ይረዳዎታል፡፡ይህን በተመለከተ ከፌደራል የስደተኞች ቢሮ መረጃ ማግኘት ይችላሉ። በአንዳንድ ከተሞች ለሴቶች ፣ መሰረተ ትምህርት ወይም ከህፃናት ማቆያ ጋር ልዩ የትምህርት አቅርቦቶች አሉ። ይህን በተመለከተ ቋንቋ ትምህርት ቤት ይጠይቁ፡፡

ሥራ እየፈለጉ ነው ወይስ ጀርመንኛዎን ለሥራ ማሻሻል ይፈልጋሉ? እንግዲያውስ የስራ ቋንቋ ትምህርት መውሰድ ይችላሉ። በትምህርቱ ላይ ለሥራዎ የሚያስፈልጎትን ጀርመንኛ መማር ይችላሉ። የሥራ ቋንቋ ትምህርት ከመውሰድዎ በፊት ጀርመንኛ መናገር ወይም የውህደት ኮርሱን ማጠናቀቅ አለቦት። የቅጥር ኤጀንሲን፣ የሥራ ማዕከሉን ወይም አሠሪዎን ይጠይቁ።

በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች

ተከተሉን