የልጅ እንክብካቤ

Schild mit Aufschrift "Kindergarten" © Goethe-Institut/ Gina Bolle

ስራ መሄድ ካለቦት ለልጅዎ እንክብካቤ ያስፈልግዎታል፡፡ እንክብካቤ ማለት፡- አንድ ሰው ልጅዎን ይንከባከባል። የተለያዩ አማራጮች አሉ፡፡ የመዋዕለ ሕፃናት፣ የመጫወቻ ቡድን፣ የወንድ ሞግዚት/የሴት ሞግዚት፣ መዋዕለ ህፃናት፣ ከትምህርት በኋላ እንክብካቤ ወይም የምሳ ሰዓት እንክብካቤ።

Audio-Player: Artikel anhören

Artikel anhören

Kinderbetreuung

የመዋዕለ ሕፃናት ማእከላት - አብረው ይጫወቱ, አብረው ይማሩ

በጀርመን ብዙ ልጆች በመዋዕለ ሕጻናት ይቆያሉ፡፡ እዚያም ከሌሎች ልጆች ጋር ይጫወታሉ አዳዲስ ጓደኞችም ያፈራሉ። ልጆ ከእርስዎ ጋር ቤት ውስጥም መቆየት ይችላል። ነገር ግን የመዋዕለ ሕፃናት ብዙ ጥቅሞች አሉት፡፡ልጅዎ እዚያ ጀርመንኛ እና ሌሎች ነገሮችን ይማራል።

ከተሞች እና ማህበረሰቦች እንደ መጠናቸው በርካታ የመዋዕለ ሕፃናት አሏቸው። ነገር ግን በቤተክርስቲያን ወይም በሌሎች ድርጅቶች የሚተዳደሩ የመዋዕለ ሕፃናት ለምሳሌ ካሪታስ አሉ፡፡ የግል መዋዕለ ሕጻናት እና በወላጆች ተነሳሽነት የተመሰሩት መዋዕለ ሕፃናት አሉ። በወላጅ ተነሳሽነት የተመሰረቱት በወላጆች ትብብር ነው። አንዳንድ የመዋዕለ ሕፃናት ሁለት ቋንቋ ተናጋሪዎች ናቸው። ሁለት ቋንቋዎች ለምሳሌ ጀርመንኛ እና ስፓኒሽ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ልጆቹ ቀኑን ሙሉ ከቤት ውጭ የሚገኙባቸው የመዋዕለ ሕፃናት ማቆያዎችም አሉ።

ክፍያ መጠን

አብዛኞቹ የመዋዕለ ሕፃናት ክፍያ ይኖራቸዋል። የግል መዋዕለ ሕጻናት ብዙ ጊዜ ከማዘጋጃ ቤት የመዋዕለ ሕፃናት የበለጠ ክፍያ ይኖራቸዋል፡፡ የክፍያ መጠን በፌዴራል ግዛቶች መከከል ይለያያሉ፡፡ ሁሉም ሰው ተመሳሳይ የክፍያ መጠን መክፈል የለበትም፡፡ ይህም በብዙ ነገሮች ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ለምሳሌ ምን ያህል ገቢ እንደሚያገኙ፤ ልጅዎ ስንት አመት እንደሆነ እና ህጻኑ በመዋዕለ ሕፃናት ውስጥ ስንት ሰዓት እንደሚቆይ መሰረት ያደረገ ነው ፡፡ በአንዳንድ ግዛቶች እና ከተሞች የህጻናት እንክብካቤ ከክፍያ ነፃ ነው። አንዳንድ ጊዜ ይህ በሁሉም የሕጻናት መንከባከቢያ ቦታዎች ላይ ተግባራዊ ይሆናል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ከክፍያ ነጻ የሚሆነው መዋዕለ ሕፃናት ብቻ ናቸው፡፡ አብዛኛዎቹ ልጆች በመዋዕለ ሕፃናት ሲቆዩ ምግብ እና መጠጥ ሰጣቸዋል፡ለዚህም በየወሩ ክፍያ ይኖረዋል፡፡ ነገር ግን ትንሽ ገንዘብ ካሎት ድጋፍ ያገኛሉ፡፡ በስራ ማእከል ወይም በማህበራዊ ደህንነት ቢሮ መጠየቅ ይችላሉ።

ምዝገባ

ከ 2013 ጀምሮ፣ ዕድሜያቸው ከአስራ ሁለት ወር እና ከዚያ በላይ የሆኑ ልጆች የመዋዕለ ሕፃናት ቦታ የማግኘት ህጋዊ መብት አላቸው። ይህ ማለት 1 አመት እና ከዚያ በላይ የሆናቸው ህጻናት ወላጆቻቸው ከፈለጉ ወደ መዋዕለ ሕጻናት እንዲገቡ ይፈቀድላቸዋል። በጀርመን ውስጥ በጣም ጥቂት የመዋዕለ ሕፃናት ቦታዎች እና በጣም ጥቂት አሳዳጊ በመኖሩ ምክንያት ልጅዎን ቀደም ብለው በተለያዩ የመዋዕለ ሕፃናት ውስጥ ማስመዝገብ አለብዎት፡፡ለልጅዎ የሚሆን ቦታ ካላገኙ ቅሬታ ማቅረብ ይችላሉ። ይህ ማለት ለምሳሌ፣ በሕጻን እንክብካቤ ቦታ እጦት ምክንያት ስራ መስራት ካልቻሉ ወይም የስራ ሰት መቀነስ ግዴታ ከሆነቦት አልያም ለልጅዎ መዋዕለ ሕጻናት ለማግኘት ብዙ ገንዘብ ሊያስወጣዎት እንደሚችል ታሳቢ በማድረግ ፍርድ ቤቱ ገንዘብ እንዲያገኙ ሊወስን ይችላል ።

ህፃናት እስከ 3 ዓመት ድረስ

እርስዎ እና የትዳር አጋርዎ ይሰራሉ ? ትንሽ ልጅ (የወራት ልጅ እስከ 3 አመት እድሜ ) አለዎት? እንግዲያውስ ልጅዎን በመዋዕለ ጨቅላ ሕፃናት ውስጥ ማስቀመጥ ይችላሉ፡፡ በመዋዕለ ጨቅላ ሕጻናት ውስጥ በጣም ጥቂት ቦታዎች አሉ። ብዙውን ጊዜ ወላጆች ገና በነብሰ ና ወቅ ልጆቻቸውን ያስመዘግባሉ፡፡

ልጅዎ ከወንድ ሞግዚት ወይንም ሴት ሞግዚት ዘንድ ማቆየትም ይችላል። እንክብካቤውም በሞግዚቱ ወይም በሞግዚቷ ቤት ውስጥ ነው፡፡ እነሱም የሚንከባከቡት ትንሽ የልጆች ቁጥር ብቻ ነው።

በየቀኑ የልጆች እንክብካቤ አያስፈልጎትም? ነገር ግን ልጅዎ ከሌሎች ልጆች ጋር እንዲገናኝ ይፈልጋሉ? የመጫወቻ ቡድኖችም አሉ። ወላጆች እና ልጆች አንድ ላይ ሆነው እነዚህን ቡድኖች ላይ መሳተፍ ይችላሉ። ወይም ልጆቹ እዚያ እንክብካቤ የሚያገኙት ለጥቂት ሰዓታት ብቻ ነው። ለትናንሽ ልጆች እንደ መዋኘት፣ አብሮ መዝፈን ወይም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የመሳሰሉ ሌሎች ለወላጅ እና ልጅ የሚሆኑ አቅርቦቶች አሉ። በዚያውም ከሌሎች ወላጆች ጋር መተዋወቅ ይችላሉ፡፡

መዋዐለ ሕጻናት

ከ 3 ዓመታቸው ጀምሮ ትምህርት እስኪጀምሩ ድረስ ልጆች ወደ መዋዐለ ሕጻናት ይሄዳሉ፡፡ እዚያ መጫወት, መዘመር, ቀለም መቀባት እና የእጅ ሥራዎችን መሥራት ይችላሉ፡፡ አብዛኞቹ መዋለ ህፃናት ትልቅ የአትክልት ቦታ አላቸው። በብዙ መዋለ ህፃናት ውስጥ አስተማሪዎቹ ልጆቹን በበጋ ወቅት ወደ ተፈጥሮ ይወስዳሉ ወይም ሽርሽር ይሄዳሉ፡፡

መዋዕለ ህፃናት ለትምህርት ቤት አስፈላጊ ዝግጅት ስለሚያደርግ ሁሉም ልጆች ቢያንስ በ 5 ዓመታቸው ወደ መዕዋለ ህፃናት መሄድ አለባቸው፡፡ ብዙ መዋዕለ ህፃናት የቋንቋ ድጋፍ ይሰጣሉ። ጀርመንኛ በደንብ የማይናገሩ ልጆችን ይረዳሉ። አንዳንድ ጊዜ ጀርመንኛ ለጀርመን ልጆች እንኳን አስቸጋሪ ነው፡፡ ለምሳሌ, አስተማሪዎቹ ከልጆች ጋር የቋንቋ ጨዋታዎችን ይጫወታሉ፤ ያነባሉ እና ታሪኮችን ያወራሉ፡፡

በትናንሽ ከተሞች ውስጥ መዋዕለ ሕፃናትም አሉ። ልጅዎን ለመዋዕለ ሕፃናትም ቀድመው ያስመዝግቡት። በነዚህ ከተሞችም ብዙ ቦታዎች የሉም። በመዋዕለ ሕፃናት ውስጥ ልጅዎ ጓደኞችን ያገኛል፤ ጀርመንኛ ይናገራል እና ከአዲሱ ሀገር ጋር በፍጥነት ይተዋወቃል፡፡

አንዳንድ መዋዕለ ሕጻናት የሚከፈቱት እስከ እኩለ ቀን ድረስ (ከጠዋቱ 1፡00 ወይም 2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 6፡ 00 ወይም 7፡00 ) ብቻ ነው፡፡ ሌሎች መዋዕለ ሕጻናት ቀኑን ሙሉ (ከጠዋቱ 1፡00 ወይም 2፡00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 10፡00 ወይም 11፡00) ክፍት ናቸው።

እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ልጆች

ዕድሜያቸው 6 ወይም 7 የሆኑ ልጆች ወደ ትምህርት ቤት መሄድ አለባቸው፡፡ ትምህርት ቤት መገኘት ግዴታ ነው። ስለዚህ ጉዳይ በእኛ የመረጃ ጽሑፍ „የትምህርት ስርዓት“ ውስጥ ማንበብ ይችላሉ፡፡ ቀኑ ሙሉ ስራ የሚውሉ ከሆነ ልጅዎ ለሙሉ ቀን ትምህርት ቤት ወይም ከትምህርት በኋላ ወደሚገኝ የእኩለ ቀን መቆያ ማዕከል ወይም የምሳ ሰአት እንክብካቤ መሄድ መቆየት ይችላል። ልጅዎ ብዙውን ጊዜ እዚያ ምሳ መብላት ይችላል። ልጅዎ ከትምህርት በኋላ ባለው የእኩለ ቀን መቆያ ማዕከል እስከ ቀኑ 10፡00 ወይም 11፡00 ሰዓት ድረስ መቆየት ይችላል። የእኩለ ቀን መቆያ ማዕከል ብዙውን ጊዜ ያን ያህል ረጅም አይደለም፡፡

በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች

ተከተሉን