የሙያ ስልጠና

Werkbank mit Holz, wo zwei Personen ein Holz vermessen © Goethe-Institut

በስልጠና ወቅት አንድ ሙያ ይማራሉ። ለምሳሌ እንደ ዳቦ ጋጋሪ፣ እንደ ኤሌክትሪክ መሐንዲስ፣ እንደ ነርስ፣ እንደ አትክልተኛ እና እንደ አስተማሪ ብዙ የተለያዩ የስልጠና ትምህርቶች አሉ፡፡

ቪዛ፣ ዲግሪ እና የምስክር ወረቀት

በጀርመን ሙያ መሰልጠን ይፈልጋሉ? እርስዎ ከአውሮፓ ህብረት (አህ) ወይም ከአውሮፓ ኢኮኖሚ ክልል (ኢኢኤ) አይደሉም? እንግዲያውስ ቪዛ ያስፈልግዎታል። ቪዛ በአገርዎ ካለው የጀርመን ኤምባሲ (ወይም ቆንስላ) ማግኘት ይችላሉ።

ስልጠናዎትን ጨርሰዋል? ብዙ ኩባንያዎች የተካኑ ሠራተኞችን ይፈልጋሉ። ማመልከት ይችላሉ። ብዙውን ጊዜ የምስክር ወረቀት ያስፈልግዎታል። የምስክር ወረቀቱ ስለ ትምህርትዎ ወይም ሙያዎ መረጃን የያዘ ህጋዊ ሰነድ ነው። ከአገርዎ የምስክር ወረቀቶች አሎት? እንግዲያውስ እንዲተረጎሙ እና እንዲያረጋግጡ ያድርጓቸው። የምስክር ወረቀቶቹ የሚመለከተው ህጋዊ ተቋም ጋር በመሄድ ያረጋግጡ ።ከዚያም በቀላሉ ሥራ ማግኘት ይችላሉ። ሥራ ፍለጋ በሚለው ጽሑፍ ውስጥ የበለጠ ማንበብ ይችላሉ።

የስልጠና ፍለጋ

በብዙ ኩባንያዎች እና በሁሉም መስኮች ላይ የሙያ ስልጠና መወሰድ ይችላሉ። ለስልጠና ቢያንስ የሁለተኛ ደረጃ የምስክር ወረቀት ያስፈልግዎታል። አንዳንድ ጊዜ የሁለተኛ ደረጃ ዲፕሎማ ወይም ትራንስክሪፕት ያስፈልግዎታል። (ትምህርት ቤት ስርዓት). የሚለውን ፁሁፍ ይመልከቱ፡፡ የትምህርት ቤት መልቀቂያ ሰርተፍኬት ከሌለ የሙያ ስልጠና ማግኘት በጣም ከባድ ነው። የሙያ ስልጠና ቦታ ለማግኘት ልክ ሥራ ቦታ እንደመፈለግ ማለት ነው፡፡ ማመልከቻ መጻፍ አለቦት። ሥራ ፍለጋ በሚለው ጽሑፍ ውስጥ ስለ ማመልከቻዎች እና የሥራ ፍለጋዎች ጉዳይ ተጨማሪ መረጃ እና ጠቃሚ ምክሮችን ያገኛሉ።

በእያንዳንዱ ከተማ ውስጥ የሙያ መረጃ ማእከል አለ። ሰራተኞች እዚያ ምክር ይሰጡዎታል እና የስልጠና ቦታ እንዲያገኙ ይረዱዎታል። የሙያ መረጃ ማእከል በከተማዎ በሚገኘው የቅጥር ኤጀንሲ በኩል ማግኘት ይችላሉ።

የሙያ ስልጠናው ሂደት

ሁለት ዓይነት የሙያ ስልጠናዎች አሉ፡- በት/ቤት ላይ የተመሰረተ ስልጠና እና ጥምር ስልጠና ናቸው። በት/ቤት ላይ የተመሰረተው የሙያ ስልጠና የሚሰጠው በሙያ ትምህርት ቤት ወስጥ ብቻ ነው። ይህንን ለማድረግ የትምህርት ቤት መልቀቂያ ሰርተፍኬት እና አንዳንድ ጊዜ ተጨማሪ የስራ ልምድ ለምሳሌ እንደ የስራ ላይ ልምምድ ማስረጃ ወረቀት ያስፈልግዎታል።

ጥምር የሙያ ስልጠና በኩባንያ ላይ የተመሰረተ የሙያ ስልጠና ተብሎም ይጠራል። በጀርመን ውስጥ ብዙውን ጊዜ ጥምር የሙያ ስልጠና ስርዓት አለ።ይህም ተግባራዊ ስልጠና እና የንድፈ ሐሳብ ክፍል አሎት። የተግባራዊ ስልጠናውን በቀጥታ በድርጅት ውስጥ ይሰራሉ። በተጨማሪም ወደ ሙያ ትምህርት ቤት ይሄዳሉ። እዚህ ለስራዎ ንድፈ ሃሳብ ይማራሉ። እንደ ጀርመንኛ፣ ፖለቲካ ወይም ስፖርት ያሉ የትምህርት አይነቶችን ይማራሉ።

በኩባንያው ውስጥ ተግባራዊውን ስልጠና ይወስዳሉ። በሳምንት ከ 3 እስከ 4 ቀናት በኩባንያው ውስጥ ይሰራሉ እና በሳምንት ከ 8 እስከ 12 ሰአታት በሙያ ትምህርት ቤት ውስጥ ይማራሉ። አልያም ጥቂት ሳምንታት በኩባንያው እና ጥቂት ሳምንታት በሙያ ትምህርት ቤት ያሳልፋሉ።

ከስልጠናው የመጀመሪያ አጋማሽ በኋላ መካከለኛ ፈተና መውሰድ አለብዎት። ሰልጣኞች ወይም ተለማማጆች የተማሩትን ነገሮች ያሳዩበታል። በስልጠናው መጨረሻ የማጠቃልያ ፈተና ይወስዳሉ። ከዚያም በኋላ ሰልጣኞች የስልጠና የምስክር ወረቀት ይቀበላሉ። ሥራ ለማግኘት ከፈለጉ ይህ የምስክር ወረቀት አስፈላጊ ነው። ለበለጠ መረጃ ሥራ ፍለጋ የሚለውን ጽሁፍ ይመልከቱ።

የስልጠና ቆይታ

የሙያ ስልጠና አብዛኛውን ጊዜ ከ 2 እስከ 3 ወይም 5 ዓመታት ይቆያል። ይህም በሚሰለጥኑት ሙያ ላይ እንዲሁም በትምህርት ቤት መልቀቂያዎ የምስክር ወረቀት ላይም ጭምር መሰረት ያደረገ ነው። በሁለተኛ ደረጃ ዲፕሎማ የስልጠናው ጊዜ ብዙውን ጊዜ አጭር ነው። በስልጠናው ወቅት በዓመት ቢያንስ 24 ቀናት ወይም 4 ሳምንታት የእረፍት ጊዜ ይኖርዎታል። ሆኖም ይህ ሊሆን የሚችለው የሙያ ትምህርት ቤቱ በእረፍት ላይ ሲሆን እና ሲዘጋ ብቻ ነው።

እንዲሁም በአጭር ጊዜ ውስጥ ሊማሩ የሚችሉ የሙያ ስልጠና ትምህርቶች ለምሳሌ የህፃናት እንክብካቤ፣ የአረጋውያን እንክብካቤ፣ የምግብ ዝግጅት ወይም ስነ ውበት ላይ ያተኮሩ ስልጠናዎች አሉ። እነዚህ በአብዛኛው በት/ቤት ውስጥ ላይ ብቻ የተመሰረቱ የሙያ ስልጠና ትምህርቶች ናቸው። በትምህርት ቤት ውስጥም የሙያ ስልጠናው ከ 1 እስከ 3 ወይም እስከ 5 ዓመታት ይቆያል። በከተማዎ በሚገኘው የቅጥር ኤጀንሲ ተጨማሪ ይጠይቁ።

ደሞዝ

በጀርመን ውስጥ ጥምር ሙያዊ ስልጠና ካደረጉ መጠነኛ ገንዘብ ያገኛሉ። ቀጣሪው ደሞዝ ይከፍልዎታል። ደመወዙ እንደ ሙያው እና እርስዎ በሚሰሩበት ክልል ይለያያል። ደመወዙ አብዛኛውን ጊዜ በየአመቱ ከስልጠና በኋላ ይጨምራል። ብዙ ጊዜ ደመወዙ ሁሉንም እንደ የቤት ኪራይ፣ ምግብ፣ የትርፍ ጊዜ ማሳለፊያዎች፣ የመሳሰሉ ወጪዎችን ለመሸፈን በቂ አይደለም። የገንዘብ እርዳታ ለምሳሌ የሙያ ስልጠና አበል ወይም የሙያ ስልጠና እርዳታ አለ። በከተማዎ ያለውን የቅጥር ኤጀንሲ ይጠይቁ። በትምህርት ቤት ውስጥ ብቻ ላለ ሙያዊ ስልጠና ክፍያ አያገኙም። አንዳንድ ጊዜ የትምህርት ቤት ክፍያም መክፈል ሊኖርቦትም ይችላል።

በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች

ተከተሉን