ሥራ ፍለጋ

Eingangsportal einer Agentur für Arbeit © Goethe-Institut

በጀርመን ውስጥ መሥራት ይፈልጋሉ እና ከአውሮፓ ህብረት (አህ) ወይም ከአውሮፓ ኢኮኖሚክ አካባቢ አይደሉም? እንግዲያውስ በጀርመን ውስጥ የሥራ ፈቃድ ያስፈልግዎታል።የመኖሪያ ፈቃድዎ ይህንን መረጃ ይዟል፡ እንድትሰሩ ተፈቅዶልዎታል? ምን ያህል እንዲሰሩ ተፈቅዶልዎታል?

Audio-Player: Artikel anhören

Artikel anhören

Arbeitssuche

የምስክር ወረቀቶች እና እውቅና

በአገርዎ የሙያ ስልጠና፣ የዩኒቨርሲቲ ዲግሪ ወይም የትምህርት ቤት መልቀቂያ ሰርተፍኬት አጠናቀዋል? እነዚህ የምስክር ወረቀቶች/ሰነዶች ማስተርጎም እና ማረጋገጥ ይኖርቦታል።ማረጋገጥ ማለት፡- ህጋዊ ባለስልጣን ሰነዶችዎ እውነተኛ መሆናቸውን ያረጋግጣል። ይህ በአገርዎ ባለ ባለስልጣን ቢደረግ የተሻለ ነው። አንዳንድ ጊዜ ዲግሪዎ በጀርመን ውስጥ አይሰራም። ይህንን በአገርዎ (የውጭ አገር መመዘኛዎችን እውቅና) ማረጋገጥ ይችላ።በ"ጀርመን እውቅና ማግኘት" በሚለው ድህረ ገጽ ላይ ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ። የእኛን መረጃ ንድፍ ይመልከቱ።

ሥራ መፈለግ

አብዛኛዎቹ የሥራ ማስታወቂያዎች በበይነ መረብ ላይ ይገኛሉ። ታዋቂ የስራ መግቢያዎች እዚህ አሉ፣ ለምሳሌ፡ ብዙ ጊዜ አዲስ የስራ ማስታወቂያዎችን ከስራ መግቢያ በኢሜል መቀበል ይችላሉ። አንዳንድ ጊዜ ማመልከቻውን በስራ መግቢያ በኩል መላክ ይችላሉ። በ "Xing" እና "LinkedIn" ላይ ከግለ ታሪኮ ጋር መገለጫ ይፈጥራሉ። ከዚያ ቀጣሪዎች የእርስዎን የሥራ ልምድ ማየት ይችላሉ። እንዲሁም በሙያ ሊረዱዎት የሚችሉ ብዙ ትውውቆችን ከዚያ ላይ ማግኘት ይችላሉ። አንዳንድ ጊዜ በኩባንያው መገለጫዎች ላይ ክፍት የስራ ቦታዎችን ማግኘት ይችላሉ።

እንዲሁም አንድ ኩባንያ በቀጥታ መጠየቅ ይችላሉ። አንዳንድ ጊዜ በኩባንያው ድረ-ገጽ ላይ የስራ ክፍት ቦታዎችን ማግኘት ይችላሉ። “የስራ ማስታወቂያዎች” ወይም “ክፍት የስራ ቦታዎችን”ብለው ይፈልጉ። እዚያ ምንም ክፍት የስራ ቦታዎችን አላገኙም? በራሶ ተነሳሽነት ማመልከቻ ወደ ኩባንያው መላክ ይችላሉ። ሁሉም ክፍት የስራ ቦታዎች ሁልጊዜ ማስታወቂያ አይወጣላቸውም።

በትውልድ ሀገርዎ ውስጥ ሥራ እየፈለጉ ከሆነ፣ የማዕከላዊ የውጭ እና የስፔሻሊስት ምደባ ቢሮን መጠየቅ ይችላሉ። የማዕከላዊ የውጭ እና የስፔሻሊስት ምደባ ቢሮን ለጀርመን በውጪ ሀገር የተካኑ ሰራተኞችን ይፈልጋል።

በጀርመን ከሆኑ ከሙያ መረጃ ማዕከል የፌደራል ቅጥር ኤጀንሲ መረጃ ያግኙ። እዚያም የስራ ማስታወቂያዎችንና ስለ ሙያ እና ስራ ብዙ መረጃዎችን ያገኛሉ። ግለ ታሪኮን በይነመረብ ላይ እዚያ ላይ ማስቀመጥ ይችላሉ። በአንድ ኩባንያ ውስጥ ያለው የስራ ልምምድ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል፡ ስራውን ማወቅ እና አዳዲስ ሰዎችን ሊተዋወቁበት ይችላሉ።

ነገር ግን ሌሎች አማራጮችም አሉ። በጋዜጣ ወይም በቅጥር ኤጀንሲ በኩል የሥራ ማስታወቂያዎችን ማግኘት ይችላሉ። በጋዜጣው ውስጥ አብዛኛውን ጊዜ ከክልሉ ስራዎች ብቻ ያገኛሉ።

የሙያ ምክር

በትውልድ ሀገርዎ፣ የማዕከላዊ የውጭ እና የስፔሻሊስት ምደባ ቢሮን ያግኙ።

በጀርመን ውስጥ ለስደተኞች ብዙ የምክር ማዕከላት አሉ። እንዲሁም ሥራ ለማግኘት እና ለማመልከት ሊረዱዎት ይችላሉ። በጀርመን የምክር አገልግሎት ይመልከቱ። የወጣቶች ፍልሰት አገልግሎት እስከ 27 አመት ለሆኑ ወጣቶች ልዩ ምክር ይሰጣል። በብዙ ከተሞች እና ክልሎች የእንኳን ደህና መጣችሁ ማዕከላትም አሉ። የጀርመን እና ዓለም አቀፍ ባለሞያዎችንና እንዲሁም ኩባንያዎችን ይመክራሉ። እዚያም ክልላዊ መረጃ ያገኛሉ፤ ሥራ ለማግኘት ድጋፍ እንዲሁም የብቃት ማረጋገጫ ላይ እገዛ ያገኛሉ።

ምን መሥራት እንደሚችሉ ወይም ምን መሥራት እንደሚፈልጉ እስካሁን አያውኩም? የቅጥር ኤጀንሲ የሙያ መረጃ ማዕከል የሙያ ምክር ይሰጣል። በአንዳንድ ከተሞችና ክልሎች የወጣቶች ሥራ ፈጣሪ ኤጀንሲዎችም አሉ። ወጣቶች ሥራ እንዲመርጡ ይረዳሉ። በሁሉም የፌደራል ግዛቶች ውስጥ ብዙ ጠቃሚ የምክር ማዕከላትን በ"ጀርመን ያሳኩ" መግቢያ ላይ ወይም "አስፈላጊ አድራሻዎች" በሚለው ገጽ ላይ ማግኘት ይችላሉ።

የስራ ማመልከቻ

የስራ ማመልከቻ ወደ ሥራ ገበያው ለመግባት የመጀመሪያ ደረጃ ነው። የስራ ማመልከቻ ሰነዶች በጣም አስፈላጊ ናቸው። የሽፋን ደብዳቤ (ለድርጅቱ ደብዳቤ) ፣ ግለ ታሪክ (ፎቶው አማራጭ ነው) እና የምስክር ወረቀቶችዎ (በጀርመንኛ) ያስፈልግዎታል። የቅጥር ኤጀንሲ የሙያ መረጃ ማዕከል "በጀርመን ማመልከት" በሚለው ርዕስ ላይ አውደ ጥናቶችን ያቀርባል። የስራ ማመልከቻ ምን እንደሚመስል እና ለቃለ መጠይቁ እንዴት እንደሚዘጋጁ ይማራሉ። ቁጥራቸው እየጨመረ የመጣ ቀጣሪዎች የስራ ማመልከቻዎችን በዲጂታል መልክ ለምሳሌ በኢሜል ወይም በስራ መግቢያ መቀበል ይፈልጋሉ።

መስፈርቶቹ ምን እንደሆኑ አስቀድመው ይወቁ።

በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች

ተከተሉን