ይህ በአንዳንድ ነገሮች ላይ ይወሰናል። በውሉ ላይ ለሞባይል ስልክ አቅራቢው ወርሃዊ መሰረታዊ ክፍያ ይከፍላሉ። በቅድመ ክፍያ ሞባይል አገልግሎት ተጠቃሚ ከሆኑ የሞባይል ካርድ ስልክዎ ይሞላሉ ። ከውል ጋር ያለው ታሪፍ በመጀመሪያ ሲታይ ቅናሽ ነው። ነገር ግን ሒሳቡን በጥንቃቄ ያስሉ። አንዳንድ ጊዜ መሰረታዊ ክፍያ ከጥቂት ወራት በኋላ ይጨምራል። ውሎች ብዙውን ጊዜ የአንድ ወይም ሁለት ዓመት ጊዜ አላቸው። ስለዚህ እነሱ ተለዋዋጭ አይደሉም። በምላሹ ብዙውን ጊዜ ከውሉ ጋር አዲስ የእጅ ስልክ ያገኛሉ።