ፖለቲካ እና ማህበረሰብ

Menschenmenge mit Regenbogenflagge © Goethe-Institut/ Gina Bolle

ጀርመን ዲሞክራሲያዊ ሃገር ነች። ህዝቡ ሀገሪቱን የሚያስተዳድረው ማን እና በምን አይነት ህግ ነው የሚለው ላይ በጋራ ይወስናል። ዜጎቹ መንግስትን ይመርጣሉ። ሁሉም ሰው በፖለቲካዊ ህይወት ውስጥ ለምሳሌ በማኅበራት፤ተነሳሽነት፤ በሠራተኛ ማኅበራት ውስጥ ወይም የፖለቲካ ፓርቲ ውስጥ መሳተፍ ይችላል፡፡

Audio-Player: Artikel anhören

Artikel anhören

Politik und Gesellschaft

መሰረታዊ ህግ

የጀርመን ሕገ መንግሥት መሠረታዊ ሕግ ይባላል። መሰረታዊ ህግ በጀርመን ውስጥ አብሮ ለመኖር በጣም አስፈላጊ የሆኑትን ህጎች ይዟል፡፡

ጀርመን የህግ የባላይነት ይሰፋነባት ነች። ዕድሜ፣ ጾታ፣ ዘር እና ሃይማኖት ሳይለይ ሁሉም ሰዎች በሕግ ፊት እኩል ናቸው። ማንኛውም ሰው በደል ደረሰብኝ ብሎ ካሰበ ፍርድ ቤት መሄድ ይችላል፡፡

ጀርመን የበጎ አድራጎት ሀገር ነች። መንግስት ዜጎቹን ይንከባከባል። የጤና መድህን፣ የጡረታ አበል እና ማህበራዊ ጥቅማ ጥቅሞች እንደ የስራ አጥነት አበል የመሳሰሉ አሉ። ሁሉም ሰው በጥሩ ሁኔታ መኖር አለበት፡፡

ጀርመን የፌዴራል ግዛት ነች። የተለያዩ ክፍሎች ማለትም የፌዴራል ግዛቶችን ያካትታል፡፡ እነዚህም 16 የፌደራል ግዛቶች አሉ፡፡ ባደን-ቩርትምበርግ፣ ባየርን፣ በርሊን፣ ብራንደንቡርግ፣ ብሬመን፣ ሃምቡርግ፣ ሄሰን፣ ሜክለንበርግ-ፎርፖመርን፣ ኒደርዛክሰን፣ ኖርድራይን-ዌስትፋለን፣ ራይንላንድ-ፕፋልስ፣ ዛርላንድ፣ ዛክሶ፣ ዛክሶ-አንሃልት፣ ሽሊስግ-ልሽታይን እና ቱሪንገን።እያንዳንዱ የፌደራል ግዛት የራሱ ህጎችና ደምቦች አሉት። ነገር ግን ለመላው አገሪቱም የጋራ ህጎችና ደንቦችም አሉ።

መብቶች እና ግዴታዎች

በጀርመን ውስጥ የሰዎች መብቶችና ግዴታዎች በመሠረታዊ ሕግ ውስጥ ይገኛሉ። ከእነዚህ መሠረታዊ መብቶች መካከል ጥቂቶቹ ለሁሉም ሰው ይሠራሉ። እነዚህ ሰብአዊ መብቶች ናቸው። ለጀርመን ዜጎች ብቻ የሚውሉ አንዳንድ መብቶችም አሉ። እነዚህ የዜጎች መብቶች ናቸው።

ዋና ዋና የሆኑት ግዴታዎች ለምሳሌ የትምህርት ግዴታ፣ የታክስ ግዴታዎች እና ሕጉን የማክበር ግዴታዎች ናቸው፡፡ በጀርመን ውስጥ ሕፃናት እና ወጣቶች ትምህርት ቤት መሄድ አለባቸው። ገንዘብ የሚያገኝ ማንኛውም ሰው ግብር መክፈል አለበት። ሁሉም ሰው ሕጎቹን ማክበር አለበት፡፡

እነዚህ በጣም አስፈላጊ መብቶች ናቸው፡፡
  • የሰው ልጅ ክብር፡- ለእያንዳንዱ ሰው ክብር ሊኖሮት ይገባል።
  • እኩልነት፡- ሁሉም ሰዎች አንድ አይነት መብት አላቸው። ለምሳሌ ሴቶችና ወንዶች እኩል መብት አላቸው።
  • በሕግ ፊት እኩልነት፡- ሰዎች ሁሉ በሕግ ፊት እኩል ናቸው።
  • ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት፡- ሰዎች የሚያስቡትን ነገር በነፃነት መግለፅ ይችላሉ።
  • የመሰብሰብ ነጻነት፡- ሰዎች በቡድን እንዲገናኙ ተፈቅዶላቸዋል።
  • የመንቀሳቀስ ነጻነት፡-ሰዎች በፈለጉበት ቦታ እንዲኖሩ ተፈቅዶላቸዋል።
  • የስራ ነጻነት፡- ሰዎች ስራቸውን የመምረጥ ነጻነት አላቸው።
ሌሎች መብቶች ጋብቻ እና ቤተሰብ ጥበቃ፤ የፕሬስ ነጻነት፤ የመምረጥ መብት እና የእምነት ነጻነት ናቸው፡፡

ልዩነት እና መቻቻል

በጀርመን ሁሉም ሰዎች ሃይማኖታቸውን በነጻነት እንዲመርጡ እና እንዲተገብሩ ተፈቅዶላቸዋል። በጀርመን ውስጥ አንድ ሦስተኛ የሚሆኑት በግልጽ ሃይማኖት የላቸውም። አብዛኞቹ ጀርመኖች የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች ናቸው፡፡ እነሱ የሮማ ካቶሊክ ወይም ፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ናቸው። እንደ ገና እና ፋሲካ ያሉ ብዙ የክርስቲያን በዓላት የሕዝብ በዓላት ናቸው። ይህ ማለት ብዙ ሰዎች በእነዚህ ቀናት ውስጥ መሥራት የለባቸውም ማለት ነው። ሆኖም ግን ብዙ የሌላ እምነት ተከታዮች በጀርመን ይኖራሉ።

በትምህርት ቤቶቹ ውስጥ የፕሮቴስታንት እና የካቶሊክ ሃይማኖታዊ ትምህርቶች አሉ። በአንዳንድ ትምህርት ቤቶች የኦርቶዶክስ፣ የአይሁድ እና የእስልምና ሃይማኖታዊ ትምህርቶችም አሉ። ወላጆች ልጃቸው የሃይማኖት ትምህርት መከታተል እንዳለባቸው መወሰን ይችላሉ። እንዲሁም ልጆቻቸው የትኛውን የሃይማኖት ትምህርት መማር እንዳለበት ይወስናሉ፡፡

በጀርመን ያሉ ሰዎች የጾታ ዝንባሌያቸውን በግልጽ እንዲገልጹ ተፈቅዶላቸዋል። ይህ ማለት የተመሳሳይ ጾታ ፍቅር፣ ከሁለት ጾታ ከሴትም ከወንድም ጋር የፍቅር ግንኙነት መጀመር፣ ግብረ-ሰዶማዊነት ልክ እንደ ተቃራኒ ጾታዊ የፍቅር ግንኙነት አንዱ የዕለት ተዕለት ሕይወት አካል ናቸው። የኤልጂቢቲኪው እንቅስቃሴ ዋናው ሚና ይጫወታል። ይህ ማኅበረሰብ ሴት ከሴት፣ ወንድ ከወንድ ጋር ግኑኝነት የሚያደርጉ፣ ከሁለት ጾታ ከሴትም ከወንድም ጋር የፍቅር ግንኙነት መጀመር፣ ጾታ የቀየሩ ወንድ ወደ ሴት፤ ሴት ደግሞ ወደ ወንድ እና በተመሳሳይ ጾታ መሃል የሚደረግ ጾታዊ ግንኙነት የሚያንቀሳቅስ ማኅበረሰብ ነው፡፡ ይህ ማህበረሰብ በጀርመን ውስጥ የሕግ ከለላ አለው፡፡ የኤልጂቢቲኪው እንቅስቃሴ ምልክት የቀስተ ደመና ባንዲራ ነው።

ከኦክቶበር 1 ቀን 2017 ጀምሮ የተመሳሳይ ጾታ ጥንዶች ማለትም ወንድና ወንድ ወይም ሴት እና ሴት በጀርመን ውስጥ በሕግ ማግባት ይችላሉ። ተመሳሳይ መብትና ግዴታ አላቸው። ይህ ማለት ለምሳሌ፡ ልጆችን በጉዲፈቻ እንታሳጉ ተፈቅዶላቸዋል። የትዳር አጋራቸውን ስም መውሰድ ይችላሉ፡፡ አንዳቸው ለሌላው ሁልጊዜ መተባበር አለባቸው፡፡

መብቶች ካልተከበሩ በአንዳንድ ሁኔታዎች መድልዎ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡የመረጃ ፅሑፋችንን „አድሎአዊነትን አያያዝ“የሚለውን ያንብቡ።

የፖለቲካ ቡድኖች እና ምርጫዎች

በዲሞክራሲ ውስጥ ምርጫዎች አሉ። በጀርመንም ልክ እንዲሁ ነው። ምርጫው ሚስጥራዊ፣ አጠቃላይ እና ነፃ መሆን አለበት። ህዝቡ ማን እንደሚያስተዳድረው ይመርጣል።

በጀርመን ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተለያዩ መርሃ ግብሮች እና ግቦች አሏቸው። ትላልቆቹ ፓርቲዎች ኤስፔዲ (የጀርመን ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ)፣ ሲዲዩ (የክርስቲያን ዴሞክራቲክ ህብረት)፣ አሊያንስ 90/ግሩነ፣ ኤፍዴፔ (ነፃ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ)፣ አኤፍዴ (አማራጭ ለጀርመን) እና ዲ ሊንከ ናቸው። ሌሎች ብዙ ትናንሽ ፓርቲዎች አሉ። ስለ ፓርቲዎች እና ፕሮግራሞቻቸው ተጨማሪ መረጃ በፌዴራል የሲቪክ ትምህርት ኤጀንሲ ድረ-ገጽ ላይ ማግኘት ይችላሉ።

ማን መምረጥ ይችላል? በጀርመን ለሚደረጉ ምርጫዎች ሁሉ የመምረጥ መብት አንድ አይነት አይደለም። አብዛኛዎቹ ምርጫዎች ላይ የሚሳተፍ 18 አመት የሞላው መሆን አለበት። በፌዴራል እና በፌደራል ግዛቶች ምርጫዎች ላይ ድምጽ እንዲሰጡ የተፈቀደላቸው የጀርመን ዜጎች ብቻ ናቸው። ባደን-ቩርትምበርግ፣ በብራንደንቡርግ፣ በብሬመን፣ ሃምቡርግና ሽሊስቭግሆልሽታይን የ16 አመት ታዳጊዎች በግዛት ምርጫዎች እንዲሳተፉ ተፈቅዶላቸዋል። መራጭ እንጂ ተመራጭ እንዲሆኑ አልተፈቀደም፡፡ መመረጥ የሚቻለው ከ 18 ዓመት ዕድሜ በላይ ነው፡፡

የአውሮፓ ህብረት ዜጎች በጀርመን ውስጥ ከሶስት ወር በላይ ከኖሩ በአካባቢያዊ ምርጫዎች ድምጽ መስጠት ይችላሉ፡፡ በባየርን፣ ሄሰን፣ ራይንላንድ-ፕፋልስ፣ ዛርላንድ እና ዛክሰን መራጮች 18 ዓመት የሆናቸው መሆን አለባቸው። በሌሎች የፌደራል ግዛቶች በ16 ዓመታቸው ድምጽ መስጠት ይፈቀድላቸዋል። ዕድሜያቸው 18 እና ከዚያ በላይ የሆናቸው ሁሉም የአውሮፓ ህብረት ዜጎች በአውሮፓ ምርጫ ላይ ድምጽ መስጠት ይችላሉ።

የመጡት የአውሮፓ ህብረት አካል ካልሆነ ሀገር ነው? እንዲህ ከሆነ በጀርመን ውስጥ መምረጥ አይፈቀድሎትም፡፡ ነገር ግን በሌላ መንገዶች መሳተፍ ይችላሉ፡፡ ብዙ ቦታዎች ላይ የውጭ ዜጎች ተወካዮች አሉ። አብዛኛውን ጊዜ የሚመረጡት በስደተኞች ነው። የውጭ ዜጎች ቦርድ ለስደተኞች ፖለቲካዊ ጥቅም ላይ ይሰራል። እንዲሁም ጥያቄዎች እና ችግሮች ላይ ይረዳሉ፡፡ በዚህ መልክ የውጭ ዜጎች፣ የስደተኞችንና የጀርመናውያንን የጋራ ኑሮ ለማሻሻል ይፈልጋሉ።

በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች

ተከተሉን