ኑሮ

Mehrfamilienhaus © Goethe-Institut/ Simone Schirmer

በጀርመን ውስጥ መኖሪያ ቤት ፍለጋ ላይ ኖት? በአንዳንድ ግዛቶች መኖሪያ ቤት ማግኘት ቀላል ቢሆንም በሌሎች ግዛቶች ማግኘት ደግሞ በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡ ፍለጋዎን ቀደም ብለው ይጀምሩና ተስማሚ የቤት ማስታወቂያ ካገኙ አከራዩን ወይንም አከራይዋን ወዲያውኑ ያግኙ።

መኖሪያ ቤት ፍለጋ

በበይነ መረብ ላይ መኖሪያ ቤት ለማግኘት ብዙ ግዛቶች አሉ ለምሳሌ፡- እንዲሁም በጋራ መኖሪያ ውስጥ አንድ ክፍል መከራየት ይችላሉ (WG በአጭሩ)። በጋራ መኖሪያ ውስጥ ከሌሎች ሰዎች ጋር መኖሪያ ቤቱን ይጋራሉ። የጋራ መኖሪያ ቤቱን ለምሳሌ wg-gesucht.de (የጋራ መኖሪያ ቤት ፍለጋ) በሚለው ድህረ ገጽ ላይ ማግኘት ይችላሉ። ለጊዜያዊ ኪራይ የሚሆን መኖሪያ ቤቶችም አሉ። እነዚህ መኖሪያ ቤቶች ሊከራዩ የሚችሉት ለተወሰነ ጊዜ ብቻ ነው፡፡

በተጨማሪም የመኖሪያ ቤት ማስታወቂያዎች በአብዛኛዎቹ ጋዜጦች ላይ ብዙውን ጊዜ አርብ ወይም ቅዳሜ በሚወጣው ጋዜጦች ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡ የመኖሪያ ቤት ማስታወቂያዎችም በጋዜጣው ድረ-ገጽ ላይ ይገኛሉ። ከዚህ በተጨማሪም በከተማዎ ወይም በማዘጋጃ ቤትዎ ውስጥ ባለው የመኖሪያ ቤት ጽ / ቤት መኖሪያ ቤት መጠየቅ ይችላሉ። ደላላ በፍለጋዎ ሊያግዞ ይችላል፡፡ ደላላው የመኖሪያ ቤት ካገኘሎ ለአገልግሎቱ መክፈል ይኖርቦታል። በተለምዶ ደላላው ከ2-3 ወር የቤት ኪራይ እንደ ኮሚሽን ይቀበላል።

ኪራይ እና ተቀማጭ ገንዘብ

ማስታወቂያዎቹ ላይ አብዛኛውን ጊዜ ለቤቱ ምን ያህል ኪራይ መክፈል እንዳለቦት ያሳያል ነገር ግን ያ ብዙውን ጊዜ የቤት ኪራይ ብቻ ነው። ይህም ማለት ተጨማሪ ወጪዎችን መክፈል ይኖርቦታል፡፡ ለምሳሌ, ለውሃ, ለደረጃ ቤት ፅዳትና ለቆሻሻ ፣ ለቤት ማሞቂያና ለኤሌክትሪክ ይከፍላሉ፡፡ እነዚህን የመሳሰሉ ተጨማሪ ወጪዎች መኖሪያ ቤት ኪራዩ አካል ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ሆኖም ግን መኖሪያ ቤቱ ተጨማሪ ወጪዎች አንዱ ከሌላው ይለያያል፡፡ ተጨማሪ ወጪዎች ምን እንደሚጨምሩ እና ሌላ ምን መክፈል እንዳለቦት አከራዮን ይጠይቁ ።

የቤቱ ኪራይና ተጨማሪ ወጪዎች ጋር በአንድ ላይ ሞቃት ኪራይ ይባላሉ። በወሩ መጀመሪያ ላይ ሁል ጊዜ ሙሉውን ኪራይ ለአከራይ ይከፍላሉ።

በተለምዶ መኖሪያ ቤቶቹ የተሟላ የቤት እቃ አይኖራቸውም፡፡ነገር ግን ብዙ ጊዜ የማዕድ ቤት አለ፡፡ብዙውን ጊዜ መኖሪያ ቤቶቹ ውስጥ ላሉ ወይም የቀድሞው ተከራይ ለሆኑ ዕቃዎች ለምሳሌ እንደ ማቀዝቀዣ መክፈል ይኖርቦታል፡፡ ይህ ማስለቀቂያ ገንዘብ ይባላል። .

ብዙ ጊዜ አከራይ ተቀማጭ ገንዘብ እንዲከፍሉ ይፈልጋል። ይህም ተቀማጭ ገንዘብ ቢበዛ የሶስት ወር የቤት ኪራይ ነው። ቤቱን ለቅው ሲወጡ ተቀማጩ ገንዘብ ተመላሽ ይደረግሎታል። የመኖሪያ ኪራይ በጣም ከፍተኛ መሆኑን ለማየት ከፈለጉ የኪራይ መረጃ ጠቋሚውን (Mietspiegel) በበይነ መረብ ማየት ይችላሉ:: ለእያንዳንዱ ከተማ አማካኝ የኪራይ ዋጋዎችን ከዚያ ላይ ማግኘት ይቻላል፡፡ ‘‘Mietspiegel" የሚለውን ቃልና የከተማውን ስም ይስጡ።

በዓመቱ መጀመሪያ ላይ ምን ያህል ውሃ፣ ኤሌትሪክ ወይም ጋዝ እንደሚያስፈልግ አይታወቅም። በየወሩ ቅድመ ክፍያ የሚከፍሉበት ምክኒያትም ይህ ነው። በዓመቱ መጨረሻ ላይ እንደአጠቃቀሞ ቀሪ ገንዘብዎን ተመላሽ ይደረግሎታል አልያም ለተጠቀሙበት አገልግሎት ተጨማሪ መክፈል ይኖርቦታል፡፡

የኪራይ ውል

ስለ ኪራይ እና ተቀማጭ ገንዘብ ሁሉም መረጃ በኪራይ ውል ውስጥ ተቀምጧል። በተጨማሪ መኖሪያ ቤቱን ለቅው ሲወጡ ማደስ ይኑርቦት ወይንስ አይኖርቦት በስምምነቱ ወስጥ ይካተታል። ወደመኖሪያ ቤቱ ሲገቡ ብዙ ጊዜ የርክክብ ስምምነት መፈረም አለብዎት፡፡ ለምሳሌ የርክክብ ስምምነቱ ላይ በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ የተበላሸ ነገር እንዳለ ይገልጻል፡፡ይህም የተበላሸ ነገር በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ ካለ እርስዎ እና አከራዮ እንዳላደረጉት በእርግጠኝነት ያውቃሉ። ከመፈረምዎ በፊት የኪራይ ውል የርክክብ ስምምነቱን በጥንቃቄ ያንብቡ።

መኖሪያ ቤቱን ለመልቀቅ ከፈለጉ፣ አብዛኛውን ጊዜ ከ 3 ወራት በፊት ማሳወቅ ይኖርቦታል። ይህ የማሳወቂያ ጊዜ ይባላል። ድርብ ኪራይ እንዳይከፍሉ የማሳወቂያ ጊዜውን ሁልጊዜ ከግምት ውስጥ ያስገቡ። ይህንን ለማድረግ በወሩ መጨረሻ ላይ ለአከራዩ ደብዳቤ መጻፍ አለብዎት።

የመኖሪያ ቤት የመተዳደሪያ ደንብ

ከጎረቤቶችዎ ጋር ግጭቶችን አይፈልጉም? አንዳንድ የመኖሪያ ቤት የመተዳደሪያ ደንቦችን ያስተውሉ፡ ፡በተለምዶ ከምሽቱ 04፡00 ሰዓት እስከ ጧት 01፡00 እና ምሳ ሰዓት 07፡00 እስከ 9፡00 እረፍት ጊዜያቶች ናቸው። በእነዚህ ሰዓታት ላይ የተጋነነ ጩኸት መኖር የለበትም፡፡ እሁድ እና በበዓላት ቀኑን ሙሉ የእረፍት ጊዜ ነው፡፡

በጀርመን ውስጥ ለወረቀት እና ለካርቶን, ለፍራፍሬ እና ለአትክልት ቅሪቶች እና ለሌሎች ቆሻሻዎች የተለያዩ የቆሻሻ ማጠራቀሚያዎች አሉ፡፡ ብዙውን ጊዜ በቤቱ ፊት ለፊት የቆሻሻ ማጠራቀሚያዎች አሉ፡፡ እዛ ቆሻሻውን መጣል ይችላሉ፡፡ የመስታወት ወይም የኤሌክትሪክ መሳሪያዎች ወደ ልዩ የመሰብሰቢያ ቦታዎች ወይም መያዣዎች መወሰድ አለባቸው፡፡ በቢጫ ከረጢት ወይም በቢጫ ማጠራቀሚያ ውስጥ የፕላስቲክ ፣ የቆርቆሮ እና የማሸጊያ ቆሻሻዎችን መጣል ይችላሉ ። በከተማው ውስጥ ብዙውን ጊዜ የፕላስቲክ እና የማሸጊያ ቆሻሻን እንደገና ጥቅም ላይ ለማዋል በአቅራቢያ ወደሚገኝ ቦታ ማምጣት ይኖርቦታል። ከከተማዎ ወይም ከማዘጋጃዎ የበለጠ መረጃ ያገኛሉ።

ሌሎች ተጨማሪ የመተዳደሪያ ደንቦችን ከመተዳደሪያው ደንቦች ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ለምሳሌ: በመኖሪያ ቤቶች ውስጥ ውሻ ወይም ድመት ይፈቀድልዎታል? ወይም በቤቱ ፊት ለፊት ያለውን መተላለፊያ ወይም የእግረኛ መንገድ ማጽዳት ይኖርቦታል?

በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች

ተከተሉን