ጤንነት

Schild vor einem Krankenhaus © Goethe-Institut/ Gina Bolle

ትንሽ የህመም ስሜት እየተሰማዎት ነው? ለምሳሌ ጉንፋን ወይም ራስ ምታት አሎት? ለመለስተኛ ህመሞች ከመድሃኒት ቤት  መድሃኒት መግዛት ይችላሉ። በጀርመን ውስጥ ብዙ መድሃኒት ቤቶች አሉ። የመድሃኒት ቤት ሰራተኞች  ለጥያቄዎቾ መልስ በመስጠት ትክክለኛውን መድሃኒት እንዲያገኙ ሊረዱዎት ይችላሉ።

Audio-Player: Artikel anhören

Artikel anhören

Gesundheit

መድሃኒት ቤት

ለብዙ በሽታዎች መድኃኒት የሚያገኙት በመድኃኒት ማዘዣ ብቻ ነው። እዚህ መድኃኒት ማዘዣ ላይ የትኛውን መድሃኒት እንደሚያስፋልጎ ተጽፏል። የመድኃኒት ማዘዣው በሐኪም መሰጠት አለበት። በመድሃኒት ማዘዣው እነዚህን መድሃኒቶች ከመድሃኒት ቤት መውሰድ እና የተወሰነውን ወጪ ብቻ መክፈል አለብዎት። ቀሪው የሚከፈለው በጤና መድህን ዋስትናው ነው።

መድሃኒት ቤቶች ብዙውን ጊዜ ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2 ሰዓት እስከ ምሽቱ 12:30 ድረስ እና ቅዳሜ እስከ ምሽቱ እስከ 1 ሰዓት ድረስ ክፍት ናቸው። በከተሞች ውስጥ ግን አንዳንድ መድኃኒት ቤቶች እስከ ምሽቱ ሁለት ሰዓት ድረስ ክፍት ናቸው። ቅዳሜ፣እሁድ እና ማታ የድንገተኛ አደጋ መድኃኒት ቤቶች አገልግሎት አለ።

የጤና መድህን ዋስትና

የጤና መድህን ዋስትና በጀርመን ላሉ ሰዎች ሁሉ ግዴታ ነው። እባክዎን መረጃውን በእኛ „የጤና መድህን ዋስትና“ የመረጃ ጽሑፋችን ያንብቡ።

የሀኪም ቀጠሮ

ህመም ይሰማዎታል ወይም የህክምና እርዳታ ይፈልጋሉ? እንግዲያውስ ከጠቅላላ ሀኪም ጋር ቀጠሮ ይያዙ። እነርሱ ስለሁሉም ህመሞቾና በሽታዎች የመጀመሪያ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣሉ። የቤተሰብች ተብለውም ይጠራሉ። ሀኪም ቤት ሄዶ መታየትም አስፈላጊ ነው። ሀኪሙ ወይም ሀኪሟ ተመልሰው ጤናማ እንዲሆኑ ሊረዱዎት ይችላሉ። እነርሱ መርዳት ካልቻሉ ወደልዩ ባለሞያ ሀኪም ይልኩዎታል።

ልጅዎ ታሟል? እንግዲያውስ ወደ የሕፃናት ሀኪም ይሂዱ። በተለምዶ ብዙውን ጊዜ ከሰኞ እስከ አርብ ብቻ ወደ ሀኪም መሄድ ይችላሉ። ለቅዳሜ፣እሁድና ማታ ተረኛ ሀኪም አለ።

ቀጠሮ ለመያዝ ወደ ክሊኒክ መደወል ይችላሉ አልያም በበይነ መረብ ቀጠሮ መያዝ ይችላሉ። ይህ በአብዛኛዎቹ ሐኪሞች ጋር ይቻላል። ቀላል እና ቀልጣፋም ነው። ወደ የሐኪም ቤቱ ድረ ገጽ ላይ ቀጠሮ ይምረጡ። ከዚያም ቀጠሮ እንደያዙ ማረጋገጫ ይደርስዎታል። ሀኪሙን መቼ ማግኘት እንደሚችሉ ይነግርዎታል። ከቀጠሮው ቀደም ብሎ በሞባይል ስልክዎ ላይ በኢሜል ወይም በጽሑፍ ቀጠሮ ማስታወሻ መልእክት ይደርሰዎታል።

የሀኪም ቀጠሮ ሲኖሮ ከጤና መድህን ዋስትና ድርጅትዎ የጤና መድህን ካርድ ያስፈልግዎታል። በመጀመሪያ ቀጠሮ ጊዜዎ ስለግል መረጃዎ መጠይቁን መሙላት ያስፈልግዎታል። ስምዎን ፣ አድራሻዎን ፣ ወዘተ ይጽፋሉ። አንዳንድ ጊዜ ሀኪም ቤቱ ምን አይነት በሽታዎች እንዳልዎ እና በቋሚ መድኃኒት እንደሚወስዱ ወይንም እንዳማይወስዱ ማወቅ ይፈልጋል።

ከተመዘገቡ በኋላ፣ በመጠበቂያ ክፍል ውስጥ ይጠብቁ። ከዚያም ስሞ ይጠራል። ይህ ብዙ ጊዜ ጥቂት ደቂቃዎችን ብቻ ይወስዳል።ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ከአንድ ሰዓት በላይ ሊወስድ ይችላል።

በሕክምና ክፍል ውስጥ ምኖትን እንደሚያሞት፤ ከመቼ ጀምሮ ህመሞ እንደጀመሮት፤ ከዚህ በፊት ይህን ህመም አጋጥሞት እንደሚያውቅ ሀኪሙ ሊጠይቆዎ ይችላል፡፡ የህመም ምልክቶችዎን በዝርዝር መግለጽ አለብዎት። ከቃለ መጠይቁ በኋላ ምርመራ ይደረግልዎታል። ሀኪሙ ምን ዓይነት ሕመም እንዳለብዎ እና ምን ማድረግ እንዳለቦት ይነግርዎታል። ብዙውን ጊዜ ሀኪሙ ወይም ሀኪሟ የመድኃኒት ማዘዣ ይሰጥዎታል። እነዚህን መድሃኒቶች ከመዳሃኒት ቤት ማግኘት ይችላሉ። አንዳንድ ጊዜ ለአዲስ ምርመራ ቀጠሮ ይሰጥዎታል።

በሕግ በተደነገገው የጤና መድህን ዋስትና ካልዎት ለሀኪም ጉብኝት መክፈል የለብዎትም። ለተጨማሪ የግል አገልግሎቶች እራስዎ መክፈል አለብዎት። የግል የጤና መድህን ዋስትና ያላቸው ሰዎች የክፍያ ደረሰኝ ከሀኪም ቤቱ ይቀበላሉ። ለምርመራው እርሶ ይከፍሉና ገንዘቡን በኋላ ከእርስዎ የጤና መድህን ዋስትና ያገኛሉ።

የሀኪም ማስረጃ

ታመው መሥራት አይችሉም? ሁልጊዜ ለአሠሪዎ ወዲያውኑ ማሳወቅ አለቦት። ለአሠሪዎ ይደውሉና ህመሙ ለምን ያህል ጊዜ ሊቆይ እንደሚችል ይንገሩት።

ሀኪም ዘንድ ሄደዋል? በህመም ምክንያት መሥራት ካልቻሉ ሀኪምዎ የህክምና ማስረጃ ይሰጥዎታል። ይህ የሀኪም ማስረጃ ተብሎም ይጠራል። በውስጡም መስራት እንደማይችሉ ይገልፃል። ቤት ውስጥ መቆየት እና ማገገም አለብዎት። በተጨማሪም በቤት ውስጥ ለምን ያህል ጊዜ መቆየት እንዳለቦት በማስረጃው ላይ ሰፍሯል። ነገር ግን ለእርሶ የሚሰጥ ምንም ወረቀት አይኖርም። ሀኪሙ የህክምና መረጃውን በቀጥታ ወደ ጤና መድህን ዋስትናው ይልካል። አሠሪዎ የሀኪም ማስረጃዎን በበይነ መረብ ላይ ማየት ይችላል።

አንዳንድ አሠሪዎች ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ የሀኪም ማስረጃ ሲጠይቁ ብዙዎቹ ደግሞ ከሦስተኛው ቀን ጀምሮ የሀኪም ማስረጃውን ይጠይቃሉ። እንዲሁም የሀኪም ማስረጃ ለማግኘት ወደ ሐኪም ቢሮ መደወል ይችላሉ። ቀላል ለሆኑ በሽታዎች ለአምስት ቀናት ሊደረግ ይችላል። ረዘም ላለ ጊዜ ከታመሙ ሐኪም ማየት አለብዎት።

ልዩ ባለሞያ ሀኪሞች

ብዙ የተለያዩ ሀኪሞች አሉ። ልዩ ልዩ የሙያ ዘርፎች አሏቸው። ለዚህም ነው ልዩ ባለሞያተኛ ሀኪሞች ተብለው የሚጠሩት። ለምሳሌ የአጥንት ቀዶ ጥገና ሀኪሞች አሉ። ከአጥንትና ከመገጣጠሚያዎች ጋር የተያያዘውን ሁሉ ለምሳሌ ክንድዎትን ከተሰበሩ ያክሞታል። ለሴቶች የማህፀን ሕክምና አሉ። ለነፍሰ ጡር ሴቶች በእርግዝና ወቅት የእርግዝና ክትትል ሕክምናና እንክብካቤ ይሰጣሉ። በተጨማሪም የአንገት በላይ እና ሌሎች ብዙ ልዩ ባለሞያ ሐኪሞች አሉ።

ብዙውን ጊዜ አጠቃላይ ሀኪሙ ወይም ሀኪሟ ወደ ልዩ ባለሞያ ሀኪም ይመራዎታል። ለዚህ በጽሁፍ የሀኪም መምሪያ ይደርስዎታል። ሀኪሞ ስለህመምዎ ከምርመራው በኋላ መረጃ ይላክለታል።

የትኛው ልዩ ሀኪም እንደሚያስፈልጎ ያውቃሉ? እንግዲያውስ በቀጥታ ወደዚያ መሄድ ይችላሉ። ወደ ልዩ ባለሞያ ሀኪም ለመሄድ መምሪያ ግዴታ አያስፈልጎትም። የጥርስ ሐኪምን ለማየት በሌላ ሐኪም መመራት አያስፈልግም።

የአዕምሮ ጤንነት

ጥሩ ስሜት አይሰማዎትም? ድካም ይሰማዎታል? አካላዊ ጤንነት በጣም አስፈላጊ ነው። ነገር ግን አካል ብቻ ሳይሆን አዕምሮም ሊታመም ይችላል። ከሀሳቦች እና ስሜቶች ጋር የተያያዘው ነገር ሁሉ ። ችግሮች፣ ቀውሶች፣ ውጥረት፣ ፍርሃት ወይም ሁከት እንድንታመም ያደርገናል። የአዕምሮ ጤንነትዎን ይንከባከቡ። እራስዎን በደንብ ይንከባከቡ። ሀዘን፣ ጭንቀት ወይም ውጥረት ከተሰማዎት እርዳታ ይፈልጉ።

የቅድመ ምርመራዎች

በቅድመ ምርመራዎች ወቅት ከባድ ህመሞች ቀደም ብለው ሊታወቁና ሊታከሙ ይችላሉ። አንዳንድ ምርመራዎች በጤና መድህን ዋስትና ይሸፈናሉ። ሌሎቹን ምርመራዎች ደግሞ በግልዎ መክፈል ይኖርቦታል።

በተጨማሪም ለልጆች የቅድመ ምርመራዎች አሉ። እነዚህም በጣም አስፈላጊ ናቸው። እንደ ኩፍኝ፣ ትክትክ ሳል እና ጉንፋን ላሉ ተላላፊ በሽታዎች ክትባቶች አሉ።መረጃውን በእኛ የመረጃ ጽሑፍ „ከልጆች ጋር መኖር" የሚለውን ያንብቡ።

ከ 35 ዓመት እድሜ ጀምሮ የኩላሊት፣ የልብ እና የደም ቧንቧ በሽታዎች፣ የስኳር በሽታ እና ካንሰር አስቀድሞ ለማወቅ ምርመራዎች አሉ። ለሴቶች የጡት ቅድመ ምርመራዎችም አሉ። ነፍሰ ጡር ሴቶች መደበኛ ምርመራዎችን ያደርጋሉ።

በቤተሰብ ውስጥ በጾታ፣ በእድሜ ወይም በህመም ላይ በመመርኮዝ የተወሰኑ ምርመራዎች አሉ። ክትባቶች አሁንም ለአዋቂዎች አስፈላጊ ናቸው። ሀኪሞን ያነጋግሩ።

ለአደጋ ጊዜ አስፈላጊ የስልክ ቁጥሮች

በጀርመን ውስጥ ያለ ማንኛውም ሰው ለፖሊስ (110) እና ለእሳት አደጋ መከላከያ ወይም የነፍስ አድን አገልግሎት (112) የአደጋ ጊዜ ቁጥር ማወቅ አለበት። እርዳታ እና ምክር ከፈለጉ ሌሎች ስልክ ቁጥሮችም አሉ። ስለዚህ ጉዳይ በጽሑፋችን „በአደጋ ጊዜ ምን ማድረግ አለቦት?“ የሚለውን ያንብቡ።

በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች

ተከተሉን