ጋብቻ

Hände mit Ringen © Goethe-Institut

በብዙ አገሮች ሰዎች የሚጋቡት ማዘጋጃ ቤት ነው። ይህ የመንግስት ተቋማዊ ጋብቻ ነው። በጀርመንም እንደዚህ ነው። ጋብቻ ጽኑ የሚሆነው በዚህ መንገድ ብቻ ነው። ከዚያ በኋላ በቤተክርስቲያን ውስጥ ማግባት ይቻላል፡፡ ሁለቱም ለመጋባት ቢያንስ 18 አመት የሞላቸው መሆን አለበት።

Audio-Player: Artikel anhören

Artikel anhören

Heirat

ጋብቻ ለሁሉም

በጀርመን ብዙ ጥንዶች ካለ ጋብቻ አብረው ይኖራሉ። ልጆች ያላቸው ጥንዶቹም በእደዚህ አይነት ሁኔታ ይኖራሉ ። ሁሉም ሰው በነፃነት መወሰን ይችላል።

ከመስከረም 24, 2009 ጀምሮ የተመሳሳይ ጾታ ጥንዶች ማለትም ወንድና ወንድ ወይም ሴት እና ሴት በጀርመንም ሊጋቡ ይችላሉ። ተመሳሳይ መብትና ግዴታ አላቸው። ይህ ማለት ለምሳሌ፡ ልጆችን በጉዲፈቻ እንዲያሳድጉ ተፈቅዶላቸዋል። የትዳር አጋራቸውን ስም መውሰድ ይችላሉ፡፡ አንዳቸው ለሌላው መደጋገፍ አለባቸው፡፡

ሰነዶች

በጀርመን ውስጥ ማግባት ይፈልጋሉ? በሚኖሩበት ማዘጋጃ ቤት ይመዝገቡ። አንዳንድ ሰነዶች -የእርስዎ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት, የልደት የምስክር ወረቀት, የምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የጋብቻ ዝግጁነት ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ያስፈልጉዎታል፡፡ ልጆች አሎት? ከሆነ የልጆትን ሰነዶች ማቅረብ ያስፈልግዎታል፡፡ ተጨማሪ ሰነዶች እንደሚያስፈልጎት ማዘጋጃ ቤት ይጠይቁ።

ከአገርዎ የመጡ ሰነዶችን ወደ ጀርመንኛ መተርጎም አለባቸው። የሰነዶቹን ትርጉሞቹ ትክክል መሆናቸውን የሚመለከትው በጠበቃ ወይንም ህጋዊ ስልጣን የተሰጠው መፈረም አለበት። ይህ የሚመለከትው ባለስልጣን ሰነዶቹን ማረጋገጥ አለበት።

ከጋብቻ በኋላ ከማዘጋጃ ቤት አዲስ ሰነድ፣ የጋብቻ የምስክር ወረቀት ይቀበላሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ፍላጎቶ ከሆነ ስለቤተሰብዎ መረጃ የያዘ የቤተሰብ መዝገብ ማግኘት ይችላሉ።

ከዚህ ቀደም በትውልድ አገርዎ ትዳር መስርተዋል? የውጭ አገር የጋብቻ የምስክር ወረቀት በማዘጋጃ ቤት ውስጥ እውቅና እዲያገኝ ማመልከት ይችላሉ፡፡ በከተማዎ ካለው በማዘጋጃ ቤት ይጠይቁ።

የሠርግ ድግስ

ብዙ ሰዎች ለሠርጋቸው ትልቅ ድግስ ያዘጋጃሉ፡፡ ሙሽራው እና ሙሽሪት ብዙ እንግዶችን ይጋብዛሉ፡፡እንደ ወላጆች፣ ወንድሞች፣ እህቶች፣ አያቶች፣ አክስቶች፣ አጎቶች፣ የአጎት ልጆች ያሉ ዘመዶች ይመጣሉ። ጓደኞችና የሥራ ባልደረቦችም ብዙ ጊዜ ይጋበዛሉ፡፡ ብዙውን ጊዜ በጀርመን ሃገር ወደ 100 የሚጠጉ እንግዶች ለሠርግ ይጠራሉ። የሠርግ ድግሶች እንዳንዳንድ አገሮች ትልቅ እይደሉም።

ምግብ፣ ሙዚቃ እንዲሁም ጭፈራ ይኖራል፡፡ ሙሽሪት እና ሙሽራው አንድ ላይ ሲጨፍሩ ሌሎች ሁሉም እንግዶች ይመለከታሉ፡፡ አብረው የሠርግ ኬክ ይቆርሳሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ለሙሽራው እና ለሙሽሪት ጨዋታዎችም አሉ፡፡ ሙሽራዋ ብዙውን ጊዜ ነጭ የሰርግ ቀሚስ ትለብሳለች፡፡ ብዙ ባለትዳሮች የሠርግ ቀለበት ይገዛሉ፡፡ እንግዶቹም ስጦታዎች ያመጣሉ፡፡ ብዙ ጊዜ ለሙሽራው እና ለሙሽሪት የገንዘብ ስጦታ ይሰጣል፡፡ እንግዶቹም ሙሽሮች ምን እንደሚፈልጉ አስቀድመው ሊጠይቁ ይችላሉ፡፡

የቤተሰብን ማስከተል

የትዳር አጋሮ በትውልድ አገሮ ነው ያሉት? ቤተሰብዎን ወደ ጀርመን ማምጣት ይችላሉ። ለዚህ የመኖሪያ ፈቃድ ያስፈልግዎታል፡፡ ይህ የሚመለከተው ባልን ወይንም ሚስትና ከ18 ዓመት በታች ለሆኑ ልጆቻቸውን ብቻ ነው። ይህ የቤተሰብን ማስከተል ወይም የትዳር አጋርን መገናኘት ይባላል። አንዳንድ ዓለም አቀፍ ሙያ ያላቸው በጀርመን ሀገር የሚኖሩ ባለትዳሮች ወላጆቻቸውን እና አማቶቻቸውን ወደ ጀርመን እንዲያመጡ ተፈቅዶላቸዋል። ይህ ከየካቲት 22፣ 2016 በኋላ የመኖሪያ ፍቃድ ከተቀበሉ ለእርሶም ተግባራዊ ይሆናል።

ለዚህም የተወሰኑ ህጎች አሉ፡፡ ቤተሰብዎን መንከባከብ መቻል አለብዎት፡፡ ለቤተሰብዎ በቤትዎ ውስጥ ለመኖሪያ የሚበቃ ቦታ ሊኖሮዎ ይገባል። የጤና መድህን ያስፈልጋቸዋል። ባል ወይም ሚስት የጀርመንኛ መሰረታዊ እውቀት ያስፈልጋቸዋል። ለዚህ የቋንቋ ሰርተፍኬት ያስፈልገዋል/ያስፈልጋታል። ይህ ሰነድ ላይ እሱ ወይም እሷ ቢያንስ የቋንቋ ደረጃ A1 እንዳላቸው ይገልጻል። ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት የጀርመንኛ የቋንቋ ሰርተፍኬት አያስፈልጋቸውም።

መለያየት እና ፍቺ

ትዳራችሁ ጥሩ አይደለም? ብዙ ጊዜ ይጋጫሉ? በመጀመሪያ የጋብቻ ምክር ወይም የባለትዳር ሕክምናን ይሞክሩ። ይህን ማድረግ አንዳንድ ጊዜ ሊረዳ ይችላል፡፡

ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ለመለያየት ወይም ለመፋታት ምክንያቶች አሉ፡፡ ፍቺ ያህል ቀላል አይደለም። በመጀመሪያ ለአንድ አመት ተለያይተው መኖር ይኖርቦታል፡፡ከራሶ ጋርም ስለ ጉዳዩ ያስቡበታል። የምክር ማዕከላት ህጋዊ ጥያቄዎችን በተመለከተ ስለልጆች ለምሳሌ ልጆቹ ከማን ጋር መኖር እንዳለባቸው ወይም ማን ምን ያህል መክፈል እንዳለበት የምክር እርዳታ ይሰጣሉ፡፡

በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች

ተከተሉን