የስራ ቦታዬ

በአዲሱ የሠራ ቦታዎ በመጀመሪያዎቹ ጥቂት ቀናት ውስጥ የሥራ ባልደረቦችዎን እና ሥራውን ይተዋወቃሉ። ብዙውን ጊዜ ከጥቂት ቀናት በኋላ ለባልደረባዎችዎ "አንተ/አንቺ " ማለት ይችላሉ፡፡ለበላይ አለቆች ማለትም ለአለቃዎ አብዛኛው ጊዜ በአንቱታ ይጠራሉ። ነገር ግን ይህ እንደ መሥሪያ ቤቱ ይለያያል፡፡ በሥራ ቦታ ጀርመንኛ ለመግባቢያ መለማመድ ይፈልጋሉ? „ጀርመንኛ መለማመድ“ የሚለውን ክፍል ይመልከቱ፡፡

Schreibtisch vor einem Fenster © Goethe-Institut/ Gina Bolle

Audio-Player: Artikel anhören

Artikel anhören

Mein Arbeitsplatz

የሰራተኞች ጥበቃ

በጀርመን ሠራተኞች የመብት ጥበቃ ይደረግላቸዋል:፡ መስሪያ ቤቱ ለሠራተኞቹ ደህንነት እና ጤና የተወሰኑ ደንቦችን ማክበር አለበት፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ለምሳሌ:_ የሥራ ልብሶች፤ መደበኛ እረፍቶች እና የሥራ ሰዓቶች ይካተታሉ፡፡ በትልልቅ ኩባንያዎች ውስጥ የሠራተኛ ማኅበር ተወካይ አለ፡፡ ችግር ካጋጠመዎት የሠራተኛ ተወካዮችን ማነጋገር ይችላሉ። የሠራተኛ ተወካይ የእርስዎን አለቃ ያነጋግራል።

የሥራ ሕግ: የሥራ ሰዓት, ​​ፍቃድ እና ሕመም

የሥራ ሰዓቱ በሥራዎ እና በሥራ ውልዎ ይወሰናል፡፡ („ሥራ መቀበል“ የሚለውን ጽሑፍ ይመልከቱ)። ለምሳሌ, በሆስፒታል ውስጥ ነርስ ከሆኑና በፈረቃ የሚሠሩ ከሆነ፣አንዳንድ ጊዜ ጠዋት, አንዳንድ ጊዜ ምሽት ወይም ማታ ይሠራሉ፡፡

በቢሮ ውስጥ ብዙ ጊዜ መደበኛ የሥራ ሰዓት ይኖርዎታል። ጠዋት ላይ ጀምርው ከ ስምንት ወይም ዘጠኝ ሰአታት በኋላ ሥራ ይጨርሳሉ። በቢሮ ውስጥ ብዙ ጊዜ ተለዋዋጭ ጊዜ አለዎት፡፡ ይህም ማለት ተለዋዋጭ የሥራ ሰዓታት ይኖሮታል፡፡ ለምሳሌ, ከጠዋቱ ሁለት ወይም ሶስት ሰዓት ላይ መጀመር እና ቀደም ብሎ ወይም ከዚያ በኋላ ምሽት ላይ መሄድ ይችላሉ፡፡ የትኛውም ሥራ ቦታ ላይ እረፍት ይኖርዎታል፡፡ ይህም ብዙውን ጊዜ የ 30 ወይም 60 ደቂቃዎች የምሳ እረፍት ነው፡፡ ብዙ አሠሪዎች ከቤት (ማለትም ከቤት) የመሥራት አማራጭ ያቅርባሉ። በተለምዶ በሳምንት ከ38-40 ሰአታት ይሠራሉ። የግማሽ ቀን ወይንም ተጥቂት ሰዓታት ሥራን የመሥራትም አማራጭ አለ፣ ለምሳሌ 50%፣ ይህም በሳምንት 20 ሰዓት አካባቢ ነው። ልጆች ካሉዎት ወይም በጎን የግል ሥራ ካሎት ይህ አማራጭ ነው። በጀርመን ዝቅተኛ ደመወዝ አለ፡፡ አሠሪዎች በሰዓት ከ12.41 ዩሮ በታች ለሠራተኞች እንዲከፍሉ አይፈቀድላቸውም ፡፡ (ከ2024 ጀምሮ)

እያንዳንዱ ሠራተኛ በዓመት የተወሰነ የአመት እረፍት ቀናት አሉት፡፡ ፈቃድዎን መጠየቅ አለብዎትና አለቃዎትም መፍቀድ አለበት። የአመት እረፍት ቀትን በቱ ውስጥ ከፋፍለው መውሰድ ይችላሉ፡፡ ብዙውን ጊዜ የአመት እረፍት ጊዜዎን በፈለጉት ጊዜ መውሰድ ይችላሉ፡፡ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ በድርጅቱ ውስጥ ብዙ ሥራ ሲኖር የአመት እረፍት መውሰድ አይችሉም። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የአመት እረፍት መውሰድ ይኖርቦታል፡፡ ምክንያቱም መሥራያ ቤቱ በሙሉ በየአመት እረፍት አይ የሚሆን ከሆነ፡፡ በየአመት እረፍት ጊዜዎ ደምወዝ ይከፈሎታል፡፡

ከታመሙ ለአሠሪዎ ወዲያውኑ ማሳወቅ አለብዎት። ይህ የሕመም እረፍት ይባላል፡፡ አብዛኛዎቹ አሠሪዎች ከታመሙ ከ 3 ቀናት በኋላ (በ 4 ኛው ቀን) የሕክምና የምስክር ወረቀት ይፈልጋሉ፡፡ („ጤና“ የሚለውን ጽሑፍ ይመልከቱ) ፡፡ አንዳንድ ጊዜ አሠሪዎች የህክምና ወረቀቱን ቀድመው ማየት ይፈልጋሉ። ወደ ሐኪም ቤት መሄድ ወይም መደወል ይችላሉ፡፡ በአብዛኛውን ጊዜ ህመምዎን በስልክ ለሐኪምዎ ሪፖርት ማድረግ ይችላሉ። ሐኪምዎ የህክምናውን ሪፖርት በዲጂታል መንገድ ለጤና መድህን ኩባንያ ያሳውቃል። ከዚያም አሠሪዎ በድህረ ገፅ ላይ ሊያያቸው ይችላል። ይህ በህግ የተደነገገ የጤና መድህን ያላቸው ሰዎችን ይመለከታል። የግል የጤና መድህን ካለዎት የህክምና ወረቀቱን በወረቀት መልክ ያስፈልግዎታል። ከዚያ ይህንን እራስዎ ማስገባት አለብዎት፡፡

የሥራ ልብስ

በአንዳንድ ሥራዎች እራስዎን ከጉዳት ለመጠበቅ ለምሳሌ በግንባታ ቦታ ላይ የሥራ ልብሶችን መልበስ አለብዎት፡፡አንዳንድ ጊዜ ዩኒፎርም ይለብሳሉ፡፡ ለምሳሌ በአውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ የሚሠሩ ከሆነ ። ወይም የድርጅትዎን አርማ ያለበት ቲሸርት መልበስ ይኖርቦታል። እርስዎ የድርጅቱ ተቀጣሪ መሆንዎን ደንበኛው የሚያየው በዚህ መንገድ ነው።

የሥራ ውል ማቋረጥ

ለድርጅትዎ መሥራት ካልቻሉ ወይም ካልፈለጉ ሥራ ለመልቀቅ ማመልከት አለብዎት። ሥራ ለማቋረጥ የሚያመለክቱት በጽሑፍ ነው። የሥራ ውል የማቋረጫ ጊዜ ገደብ አለ፡፡ በተለምዶ የማሳወቂያው ጊዜ ሶስት ወር ነው። አሠሪዎም የሠራ ውሉን ሊያቋርጥ ይችላል። እዚህም ሥራ ውል የማቋረጫ ጊዜ ገደብ ብዙውን ጊዜ ሶስት ወር ነው። በሙከራ ጊዜ ላይ ነዎት? በሙከራ ጊዜ፣ የማሳወቂያ ጊዜው ብዙ ጊዜ አጭር ነው፣ ከ2 እስከ 3 ሳምንታት። በማቋረጡ ካልተስማሙ፣ መቃወሚያ ለማቅረብ ሶስት ሳምንታት አለዎት።

ከሥራ ተባረዋል ወይስ የቋሚ ጊዜ የሥራ ውልዎ እያበቃ ነው? እንደ ሥራ ፈላጊነት መመዝገብ እና በጊዜ ለቅጥር ኤጀንሲ ሥራ አጥ መሆኖን ማሳወቅ አለበዎት። ከዚያም ለሥራ አጥ ክፍያ ማመልከት እና አብዛኛውን ጊዜ ገንዘብ መቀበል ይችላሉ፡፡ ምን ያህል ገንዘብ እና ለምን ያህል ጊዜ እንደሚከፈልዎ በበርካታ ሁኔታዎች ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ሥራዎን ራስዎን ካቋረጡ, ከቅጥር ኤጀንሲ የእገዳ ጊዜ ሊጣልቦት ይችላል፡ይህ ማለት፣ ምንም አይነት የሥራ አጥነት ክፍያ አያገኙም።

ተጨማሪ ስልጠና

አስቀድመው ስልጠና ወይም ትምህርት ካጠናቀቁ እና ለተወሰነ ጊዜ ከሠሩ, ትምህርትዎን መቀጠል ይችላሉ፡፡ እውቀትዎን እና ክህሎቶችዎን ያጠናክራሉ፣ ያሰፋሉ ወይም ያዘምናሉ። ከፌዴራል የቅጥር ኤጀንሲ መረጃ ማግኝትና ተጨማሪ ስልጠና መውሰድ ይችላሉ። የአዋቂዎች ትምህርት ማዕከላትም ሰፊ አማራጮችን ይሰጣሉ። ብዙ ጊዜ በኩባንያዎች ውስጥ ለተጨማሪ ስልጠና እድሎች አሉ፡፡ ይህን በተመለከተ አሠሪዎን ይጠይቅ።

የግል ሥራ

በግል የሚሠሩ ከሆነ፣ መቼ፣ የትና እንዴት እንደሚሠሩ ራስዎ መወሰን ይችላሉ፡ ፡ ከቤት ማለትም እቤት ውስጥ መሥራት ወይም የራስዎን ቢሮ መከራየት ይችላሉ።

ድርጅት መመስረት እና ሠራተኞች መቅጠር ይፈልጋሉ? ይህ ከሆነ ሥራዎትን በግብር ቢሮ እና/ወይም በንግድ ቢሮ መመዝገብ ማስመዝገብ። ስለመብቶች እና ግዴታዎች ማሰብ አለብዎት፡፡ ("የሠራተኛ ጥበቃ", "የሠራተኛ ህግ: የሥራ ሰዓት, የአመት እረፍት እና ህመም" እና "የሥራ ውል ማቋረጥ" ጽሑፍ ውስጥ ያሉትን ክፍሎች ይመልከቱ።)

እንዲሁም ለኩባንያዎ እና ለሠራተኞቾ አስፈላጊ መድህን ማሰብ አለብዎ፡፡ የንግድ ድርጅት መምስረት የሚለው መግቢያ ላይ ብዙ መረጃ ማግኘት ትችላለህ።

በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች

ተከተሉን