ሰራተኛ እንደመሆኖት መጠን የጡረታ ዋስትና መክፈል አለቦት። ገንዘቡ በቀጥታ ከደሞዝዎ ላይ ተቀናሽ ይደረጋል፡፡ በተጨማሪም የግል የጡረታ ዋስትና ፖሊሲዎች አሉ፡- ለምሳሌ እንደ ሰራተኛ በፈቃደኝነት የድርጅት ጡረታ መክፈል ይችላሉ። ይህ በአሰሪው በኩል ተጨማሪ ጡረታ ነው፡፡ ይህን በተመለከተ አሰሪህን ጠይቅ።
በግል ሥራ የሚተዳደሩ ሰዎች የጡረታ ዋስትና ሊኖራቸው ይችላል፣ ነገር ግን ግዴታ የለባቸውም፡፡ በግል ሥራ የሚተዳደሩ ሰዎች በአንዳንድ ሙያዎች ላይ ለምሳሌ እንደ አዋላጅ ሃኪም ወይም የዕደ ጥበብ፣ የጡረታ ዋስትና ሊኖራቸው ይገባል። እንዲሁም በግል የጡረታ ዋስትና ሊኖርዎት ይችላል።